Ante Kibre Neh Jesus our wisdom righteousness holiness and redemption by Dawit Getachew
>> YOUR LINK HERE: ___ http://youtube.com/watch?v=N_SeRiBmXrs
በክርስቶስ ኢየሱስ ለመሆን የበቃችሁት ከእርሱ የተነሣ ነው፤ እርሱ ከእግዚአብሔር ዘንድ ጥበባችን፣ ጽድቃችንና ቅድስናችን፣ ቤዛችንም ሆኖአል። እንግዲህ፣ እንዲህ ተብሎ እንደ ተጻፈ ነው፤ “የሚመካ በጌታ ይመካ።” • • 1 ቆሮንቶስ 1:30 - 31 • It is because of him that you are in Christ Jesus, who has become for us wisdom from God—that is, our righteousness, holiness and redemption. Therefore, as it is written: “Let the one who boasts boast in the Lord.” • 1 Corinthians 1:30-31 • ይሄ ቢሆንልኝ ብዪ የምመኘው • ህልሜ እውን ሆኖ መች ነው የማየው • ብዪ የማስበው የማልመው ነገር • ተሰጥቶኛል አንተን ያገኘሁኝ ቀን • ተራራ አልወጣሁ ወይ አልወረድኩኝ • ግን እንዲሁ በፀጋህ ስለወደድከኝ • ከምለምነው እና ከማስበው በላይ • ቤት ሰርተህልኛል በሰማይ • አንተ ክብሬ ነህ አንተ ጥበቤ • ቅድስናዪ የሱስ ቤዛዪ • ምን አለኝ የምሻው ከእንግዲህ • ሁሉም ተሰጥቶኛል በስምህ • ፍቅርህን እያየሁ ሁሌ አመልክሀለሁ • የእግዚአብሔር ልጅ ወድሃለሁ • አሁን ያንተ የሆነው ሁሉ የኔ ነው • ፍለጋ አልወጣም ማዶ ማዶ እያየሁ • የተቀበልከውን ሁሉ ስለሰጠኸኝ • ከአንተ የተነሳ የእግዚአብሔር ልጅ ነኝ • የተቀበልከውን ሁሉ ስለሰጠኸኝ • ካንተ የተነሳ የንጉስ ልጅ ነኝ • ነጻ ወጥቻለሁ ከሀጥያት አበሳ • ባርነቴ ቀርቷል ካንተ የተነሳ • አንተ መሀል ገብተህ እኔን አስመለጥከኝ • ውርደቴን ስድቤን ሞቴን ወሰድክልኝ
#############################
